Skip to content
zeno
Create a Station
Explore
Religious
Music
News
Podcasts
Bible
By Genre
By Location
By Language
Download App
Opens in a new window
Toggle Sidebar
zeno
DW | Amharic - News
Amharic
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Website
Episodes
Episodes
12
12 September 2026
ትኩረት በአፍሪቃ፣ የአፍሪቃ ፓርኮች አጠያያቂ ምግባር፣ የአፍሪቃዉያን ስቃይ በካምቦዲያ
አያት ቅድመ አያቶች ኡተሬሽት-ወይም ሌላ ሥፍራ-ብቻ ኔዘርላንድስ ዉስጥ ከሚገኘዉ አብያተ-መንግሥታቸዉ ሆነዉ የአፍሪቃን ካርታ እያዩ አፍሪቃን ቅኝ ለመግዛት ይወስኑ ነበር።ያሁኖቹ ደግሞ እዚያዉ አፍሪቃ (ደቡብ አፍሪቃ) ፅሕፈት ቤት ከፍተዉ በድጋፍና ርዳታ ሥም የ19ኛዉን መቶ ክፍለ ዘመን የአያት-ቅድመ አያቶቻቸዉን አገዛዝ እየደገሙት ነዉ
12 September 2026
የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ (CPJ) የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የታሰሩ ጋዜጠኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ በድጋሚ ጥሪ አቀረበ
በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ጋዜጠኞችን የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እንዲፈቱ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች በድጋሚ ጥሪ አቀረበ። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መንግሥት ከ600 በላይ እስረኞች መፍታቱን ቢያስታውቅም ጋዜጠኞቹ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና አባይ ዘውዱ አሁንም እስር ቤት ናቸው።
12 September 2026
የተሰናባቹ ዓመት እና የመጪው ዘመን ተስፋ
በኢትዮጵያ በወርሃ መስከረም መጀመሪያ ላይ የሚከበረው አዲስ ዓመት የክረምቱ ጨለማ በብርሃን የሚተካበት ነው። በዚህም አሮጌው አልፎ ወደ አዲስ ዘመን ሲገባ ብዙዎች ተስፋ እና መልካም ምኞትን ይዘው ይሻገራሉ። ለመሆኑ 2018 እንዴት አለፈ? በ2019 ዜጎች ምን ተስፋ ያደርጋሉ? ሸዋንግዛው ወጋየሁ የሀዋሳ ነዋሪዎችን አስተያየት አሰባስቧል፡፡
11 September 2026
የቀጣዩ ትውልድ አለኝታ፡ የደሴው ወጣት በጎ አድራጎት ለአዲሱ ዓመት
ወጣት መስፍን ሹመትም ባለፉት ስድስት ዓመታት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ ያልቻሉ ወላጆችን በመደገፍ ልጆች እንዲማሩ ብዙ ሠርቷል። አቶ አቡበከር ሰይድም በደሴ ከተማ ኗሪ ናቸው። ትምህርት ሊያቋርጡ የነበሩ ልጆቻቸው በወጣት መስፍን ድጋፍ ወደ ትምህርት ቤት መመለሳቸውን ይናገራሉ።
11 September 2026
በአማራ ክልል ተፈናቃዮች አዲስ ዓመትን በምን ዐይነት ስሜት ተቀበሉ?
ሐርቡ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙት መሐመድ “ተፈናቃይ” ከሚል ስም ፈጣሪ እንዲያወጣቸው ይጸልያሉ። ከራያ የተፈናቀሉ መምህር አዲስ ዓመት ሲቀበሉ “ቤቴ ናፍቆኛል፤ ልጆቼ ናፍቀውኛል” ሲሉ ተናግረዋል። በገራዶ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃይ የቀደመው የአዲስ ዓመት አከባበራቸው ከአሁኑ ባይወዳደርም “ካለን ምን አነሰን እኛ?” ሲሉ ፈጣሪያቸውን ያመሰግናሉ።
11 September 2026
የአዲስ ዓመት አካባበር በግጭት ውስጥ በቆዩ አሙሩና ኪረሙ ወረዳዎች
በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙት የአሙሩና የኪረሙ ወረዳዎች ሰላም ከራቃቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ውስጥ ናቸው። የአሙሩ ነዋሪ “ብዙ ችግሮች ቢኖሩም የጸጥታ ሁኔታው ለውጥ አሳይቷል” ብለዋል። ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱበት የኪረሙ ወረዳ ነዋሪ የጸጥታ ሁኔታው ከባለፈው ዓመት ሲነጻጸር “እምብዛም ለውጥ የለውም” ሲሉ ተናግረዋል።
06 September 2026
በኢትዮጵያ ሰላም ለምን እውን መሆን አልቻለም?
የትግራዩ ክልሉ ጦርነት በውጪ ኃይሎች ፖለቲካዊ ተፅዕኖና በአፍሪቃ ሕብረት ሽምገላ በፕሪቶሪያ ውል ቢቋጭም ግጭት ጦርነቱ ግን በአማራ ክልል በሌላ መልኩ ቀጠለ:: ኦሮሚያም ሰላም ከራቃቸው ክልሎች ቀዳሚው ነው። በርከት ባሉ መደበኛና ኢመደበኛ ታጣቂና አማጻያን ፍልሚያ የሲቪሉ ማኀበረሰብ ኑሮ ለሰቀቀን ከተዳረገ ከርሟል።
30 August 2026
የኦባሳንጆ አዲስ የሰላም ጥረት በፌደራል መንግሥትና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ምን ያህል ሊያርግብ ይችላል ?
ውጥረቱ በተባባሰበት በዚህ ሳምንት ሰኞ በአፍሪቃ ቀንድ የአፍሪቃ ኅብረት ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ መቀሌ መሄዳቸው መሰማቱ የሰላሙ ጥረት እንደገና የመንቀሳቀሱ ተስፋ ተደርጎ ተወስዷል። ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል እስካሁን ስለኦባሳንጆ ጉብኝት የተባለ ነገር የለም።
14 August 2026
ሲፒጄ በእሥር ላይ ያሉ 5 ጋዜጠኞች ይቅርታ ጠይቀው እንዲፈቱ ጫና ተደርጎባቸዋል አለ
ኢትዮጵያ ውስጥ በእሥር ላይ ያሉ አምስት ጋዜጠኞች የተከሰሱበትን የሽብር ክስ አምነው ይቅርታ እንዲጠይቁ እና እንዲፈቱ ጫና እንደተደረገባቸው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት (ሲፒጄ) ገለፀ።ሲፒጄ በእሥር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ገነት አስማው፣ዳዊት በጋሻው፣መስከረም አበራ እና አባይ ዘውዱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥሪ አድርጓል።
06 August 2026
ሲፒጄ ለ6 ሃገራት ጋዜጠኞች እውቅና ሲሰጥ በኢትዮጵያ የታሠሩት እንዲፈቱ መጠየቁ
መቀመጫውን ኒዮርክ ያደረገው የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ በእንግሊዝኛ ምህጻሩ ሲፒጄ ለስድስት ሃገራት ጋዜጠኞች እውቅና ሰጠ። 16ቱ የታሰሩ ኤርትራውያን ጋዜጠኞች ናቸው። ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተው ዓለም አቀፍ ተቋም ኢትዮጵያው ውስጥም በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ጋዜጠኞችን እንዲፈቱ ለሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጥሪ አቅርቧል።